| Is |
Singer Artist Musician |
|
| From | Ethiopia | |
| Type |
Arts Music |
|
| Gender | male | |
| Instruments: |
|
ፀሐይ ዮሐንስ (፲፱፻፶፬ ዓ.ም. ተወለደ) የኢትዮጵያ ታዋቂ ዘፋኝ ሲሆን ብዙ ዘመናዊ የሙዚቃ ስራወችን በማቅረብ ይታወቃል።
የሕይወት ታሪክ
ፀሐይ ዮሐንስ በ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. በኤርትራ ክፍለ ሀገር አሥመራ ከተማ ተወለደ። ፀሐይ ከአባቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት የሙዚቃ ችሎታውን ለማዳበር ቻለ። የ፭ኛ ክፍል ተማሪ እያለ በአብዮቱ ወቅት ፷ ሺህ ተማሪዎች ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ለዕድገት በሕብረት ዘምተው ሳለ «በርታ ዘመዴ ዘማቹ ጓዴ» የተሰኘው የመጀመሪያውን ሙዚቃ ለሕዝብ በማቅረብ በወቅቱ ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል።
ከዚያም መሀይምነትን ለማጥፋት የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ በታወጀበት ጊዜ «ማንበብና መፃፍ» የተሰኘው ዘፈኑ በጣም ቀሽቃሽና አስተማሪ ስለነበር ፀሐይን ይበልጥ እንዲታወቅ አድርጎታል።
ከእነዚህም ማህበራዊ ሕይወትን ከሚገልፁት በተጨማሪ በ፲፱፻፸፭ ዓ.ም. ካሰማቸው ዘፈኖቹ ውስጥ «ፍንጭትዋ»፣ «ያዝ ያዝ» እና «ጡር ነው» የተሰኙት በሕዝቡ ዘንድ ውዴታን ያገኙ ነበሩ። ፀሐይ አሁንም ቢሆን የተለያዩ ዜማዎችን በመዝፈን በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆት ያለው አርቲስት ነው።
የሥራዎች ዝርዝር
- ፲፱፻፸፬ ተይ ሙኒት
- ፲፱፻፸፭ ፍንጭትዋ
- ፲፱፻፸፯ ሳብ ሳም
- ፲፱፻፸፱ ጡር ነው
- ፲፱፻፹፪ ተባለ እንዴ
- ፲፱፻፹፭ ኢትዮጵያ
- ፲፱፻፹፱ ያላንቺማ
- ፲፱፻፺፪ ጀመረች
- ፲፱፻፺፬ ለትንሽ
- ፲፱፻፺፱ ሳቂልኝ